ሀድያ ሆሳዕናዎች የሦስት ተጫዋቾች ውል አራዘሙ

አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እና የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ከሚገኙ ክለቦች ውስጥ የሚጠቀሱት ሀድያ ሆሳዕናዎች አሁን ደግሞ የታዳጊ ቡድናቸው ፍሬ የሆኑ ሦስት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል። የፊት መስመር ተጫዋቾቹ ታሪኩ ፀደቀ እና ደስታ ዋሚሾ እንዲሁም አማካዩ ሱራፌል ተመስገን ውላቸው ለማራዘም የተስማሙ ተጫዋቾች ናቸው።

