ግብ አስቆጣሪው ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ከብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደረሰው

ግብ አስቆጣሪው ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ከብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደረሰው

ከሰዓታት በፊት ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋናው ቡድን ማደጉን መረጃ አጋርተናችሁ የነበረው ብሩክ ዘላለም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶታል

በኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ17 ዓመት በታች ጀምሮ እስከ 20 ዓመት ቡድን ድረስ ቆይታ ካደረገ በኋላ ዛሬ ረፋድ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋናው ቡድን ማደግ የቻለው በውድድር ዓመቱ ስምንት ግቦች ማስቆጠር የቻለው ግብ ጠባቂው ብሩክ ዘላለም ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ ደርሶታል።

ከግብ ጠባቂነቱ በተጨማሪ ከቆሙ ኳሶችን ግቦችን የማስቆጠር ብቃት ያለውና ከዚህ ቀደም ከ17 ዓመት በታች ውድድር የዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማት ያገኘው ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ከቢንያም አብርሀ ፣ ዳዊት ካሳው ፣ አሚር ሚስባህ ፣ ቸርነት ኡፋይሳ ፣ ብሩክ እይላቸው እና ቅዱስ ዳዊት ቀጥሎ ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ የተደረገለት ታዳጊ ተጫዋች ሆኗል።