ቻምፕዮኖቹ ግብ ጠባቂ አስፈረሙ

ቻምፕዮኖቹ ግብ ጠባቂ አስፈረሙ

የካፍ ቻምፕዮንስ ሊግ ተሳታፊው ሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ አስፈረመ

የ2018 የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በማሸነፍ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ መድረክ የሚሳተፉትና በመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ ከቻዱ ኤግሎስ ጋር የተደለደሉት ሲዳማ ቡናዎች ግብ ጠባቂው ቼክ ንዶዬ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

የሴኔጋል ዜግነት ያለውና ከዚህ ቀደም በ ኤ ኤስ ካምበሬን ፣ ጃራፍ ፣ ሶናኮስ እና ሬናሳንስ መጫወት የቻለው ግብ ጠባቂው በጃራፍ ቆይታው የሴኔጋል ሊግ አንድ እና የሴኔጋል ዋንጫ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ከ2019 ጀምሮ የሀገሩ ሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ማግልገል ጀምሮ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ብሔራዊ ቡድኑን ወክሎ ተካፍሏል።

በዝውውር መስኮቱ ስማቸው ከተለያዩ ግብ ጠባቂዎች ጋር ሲያያዝ የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች በስተመጨረሻም በሴኔጋል ሊግ አንድ ጥሩ ብቃት ካላቸው ግብ ጠባቂዎች አንዱ የሆነውን ቼክ ንዶዬ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።