👉 “የክለቡ ዕቅድ ስለተመቸኝ ነው ውሌን ለማራዘም የቻልኩት” አንተነህ ተፈራ

👉 “የክለቡ ዕቅድ ስለተመቸኝ ነው ውሌን ለማራዘም የቻልኩት” አንተነህ ተፈራ

“የክለቡ ዕቅድ ስለተመቸኝ ነው ውሌን ለማራዘም የቻልኩት” አንተነህ ተፈራ

ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ቀሪ አንድ ዓመት እያለው ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ከተስማማው አንተነህ ተፈራ ጋር ቆይታ አድርገናል።

አስቀድመን ባጋራናችሁ መረጃ መሠረት አንተነህ ተፈራ ዘንድሮ በአጋማሹ ከሸገር ወደ ባህር ዳር ሲመጣ ለጣና ሞገዶቹ ለአንድ ዓመት ለስድስት ወር ፈርሞ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ምንም እንኳን አንተነህ ለባህር ዳር ለመጫወት ቀሪ አንድ ዓመት ቢኖረውም ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማለትም እስከ 2020 ሰኔ 30 ቀን ለመቆየት አዲስ ውል ማሰሩን ገልፀንላቹሁ ነበር።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ውል ያለው ተጫዋቾች በውል ላይ ውል ማራዘም ብዙም ያልተለመደ መሆኑን ተከትሎ ሶከር ኢትዮጵያ ከአንተነህ ተፈራ ጋር ይህን ለማድረጉ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠይቀዋለች።

“አዎ ብዙም ያልተለመደ ሊሆን ይችላል። ግን እንደሚታወቀው አሰልጣኝ ደግአረገ ውሉን አራዝሟል። አሰልጣኙም በክለቡ ቀጣይ ሊሠራ ስላሰባቸው ዕቅዶች ጠርቶ ሲነግረኝ እና የዚህ ዕቅድ አካል ሆኜ አብሬው በመቆየት እንድሠራ ሲጠይቀኝ፣ በተጨማሪም የክለቡ አመራሮች ክለቡን ማድረስ የሚፈልጉትን ጥሩ ሀሳቦች ሲነግሩኝ በሙሉ ፍላጎት በጣም ደስ ብሎኝ የክለቡ ዕቅድ ስለተመቸኝ ነው ውሌን ለማራዘም የቻልኩት።” ብሎናል