ሁለት ተጫዋቾች ከአሳዳጊያቸው ጋር ለመቀጠል ውላቸውን አራዘሙ።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ የሁለት ተስፈኞች ውል አራዝመዋል። ከአሳዳጊ ክለባቸው ጋር ለመቀጠል ከስምምነት የደረሱት ደግሞ ወጣቱ የቀኝ መስመር ተከላካይ ናሆም ኃይለማርያም እና ግብ ጠባቂው ናትናኤል ኪዳነ ናቸው።
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ተገኝተው የበርካታ ተጫዋቾች ውል ያፀደቁት ወልዋሎዎች በነገው ዕለት የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ምዘገባቸውን በማጠናቀቅ የተጨማሪ ተጫዋቾች ውል በፌዴሬሽኑ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

