አዲስ ግደይ በይፋ የዐፄዎቹ ተጫዋች ሆኗል

አዲስ ግደይ በይፋ የዐፄዎቹ ተጫዋች ሆኗል


ከቀናት በፊት እንደነገርናቹሁ አዲስ ግደይ በይፋ ዐፄዎችን ተቀላቅሏል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አስራ አንድ ጎሎችን በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ የነበረው አዲስ ግደይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ቀሪ የአጭር ጊዜ ውል ቢኖረውም ክለቡ እርሱን ለማቆየት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ እና ፋሲል ከነማ የተጫዋቹ ፈላጊ እንደሆነ ድርድሩም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳለ እና ለዐፄዎቹ የመፈረም ዕድሉ ሰፊ እንደሆነ ገልፀን ነበር።

አሁን ባገኘነው መረጃ አዲስ ግደይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መለያየቱን ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መዕልክት አረጋግጦልናል። ይህን ተከትሎ ወደ ፋሲል ከነማ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የህክምና ምርመራውን ያደረገ ሲሆን ለሁለት ዓመት ያደረገውን ስምምነት ሰኞ ፌዴሬሽን በመገኘት ዝውውሩ ይፋ እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል።