በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ጊት ጋት ኮች ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ ለማምራት ተስማምቷል።

ከስድስት ዓመታት የሲዳማ ቡና ቆይታ በኋላ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከምዓም አናብስት ጋር ቆይታ ያደረገው የመሀል ተከላካዩ ጊት ጋት ኮች ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።
በክለብ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡናና መቐለ 70 እንደርታ ቆይታ ያደረገው እንዲሁም የመጀመሪያ ጨዋታውን ካደረገበት ግንቦት 22 2014 ዓ.ም ጀምሮ በቻን ጨምሮ በዓለም ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ያገለገለው ተከላካዩ አሁን ደግሞ ከመቐለ 70 እንደርያ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ የዕረፍት ጊዜውን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ጊት ወደ ሀምራዊ ለባሾቹ ለማምራት የቅድመ ስምምነት የፈረመ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በይፋ ፌርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

