በሻሸመኔ ከተማ ቆይታ የነበረው አጥቂ ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል

ቡድናቸውን ለማጠናከር እየሰሩ ያሉት በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚሰለጥኑት የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፕዮኖቹ ኢትዮጰያ መድኖች አሁን ደግሞ ወጣቱን አጥቂ ሙሐባ አደምን ማስፈረም ችለዋል።
በወንዶ ገነት ከተማ የተገኛው እና ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን የተጫወተው የቀድሞው የመቻል አጥቂ አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሻሸመኔ ከተማ ድንቅ ጊዜን አሳልፎ ወደ ኢትዮጵያ መድን ለማምራት ፌርማውን ማኖሩ አውቀናል።

