ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አማካዩን ወደ ስብሰባቸው ቀላቅለዋል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአዲሱ የውድድር ዘመን ስብስቡን ለማጠናከር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቀጠል አማካዩን አናንያ ጌታቸውን በይፋ ማስፈረም ችሏል። የእግር ኳስ ህይወቱን ከአውስኮድ ተስፋ ቡድን የጀመረው አናንያ በመቀጠል በጅማ አባ ጅፋር፣ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በባህር ዳር ከተማ ተጫውቶ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የሀምራዊዎቹን ማሊያ ለመልበስ ፊርማውን አኑሯል።
አማካዩ በከፍተኛ ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር በነበረው ጥሩ ቆይታ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ጥሪ ተደርጎለት ለብሔራዊ ቡድኑ መጫወቱም ይታወሳል።

