ኢብራሂም ዳንላድ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

ኢብራሂም ዳንላድ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

በኢትዮጵያ ቡና ቆይታ የነበረው ጋናዊ አዲስ ክለብ አገኘ

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ቆይታ የነበረው ጋናዊው ግብ ጠባቂ ኢብራሂም ዳንላድ ከሁለት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ አሻንቲ ኮቶኮ መመለሱ በጋና ታማኝ ከሚባሉ ጋዜጠኞች አንዱ የሆነው ሻባን መሐመድ ገልጿል።

ላለፉት ሳምንታት ከቀድሞ ክለቡ አሻንቲ ኮቶኮ ጋር ልምምድ በመስራት ላይ የቆየው እና ክለቡ ቤናብ ከተባለ ክለብ ጋር ባደረገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የተሳተፈው ግብ ጠባቂው ከደቂቃዎች በፊት የቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡና አመስግኖ ከክለቡ ጋር መለያየቱ ይፋ ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ የሀገሩን ክለብ አሻንቲ ኮቶኮ መቀለቀሉ ተገልጿል።

በሀምሳ አምስት ጨዋታዎች ቡናማውን መለያ የለበሰው ይህ ጋናዊ ከዚህ ቀደም በኪንግ ፋይሰል እና በርኩም ቼልሲ ጨምሮ ከ17 ዓመት በታች ጀምሮ እስከ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ሀገሩን ጋና ማገልገል ችሏል።