አቶ ኢሳይያስ ጅራ ብቸኛ ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው ወደ ምርጫው ይቀርባሉ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የወቅቱ የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ለዕጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡት ብቸኛ ግለ ሰብ መሆናቸው ገልጿል።
ፌደሬሽኑ ይፋ ባደረገው መሰረት የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሐምሌ 22 ለፌዴሬሽኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ለፕሬዝዳንትነት እና በፕሬዝዳንቱ አቅራቢነት የሚመረጡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከነ ተጠባባቂያቸው እስከ ነሐሴ 4 ድረስ ለፌዴሬሽኑ ፅሕፈት ቤት እንዲልኩ እንዳሳወቀ ገልጿል።
በዚህ መሰረት ኮሚቴው ነሐሴ 5 ፣ ነሐሴ 11 እንዲሁም ነሐሴ 13 ባደረጋቸው ስብሰባዎች የቀረቡ እጩዎችን ሰነድ የምርመራ እና የማጣራት ተግባር አከናውኖ አቶ ኢሳይያስ ጅራ ለዕጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡት ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን አሳውቋል።

