የቢጫዎቹ የኮንፌደሬሽን ካፕ ማጣሪያ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታወቁ

የቢጫዎቹ የኮንፌደሬሽን ካፕ ማጣሪያ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታወቁ

ወልዋሎዎች ከሱዳኑ ሂላል አልሳሕል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ለመምራት የተመደቡ ዳኞች ታውቀዋል

በካፍ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክለው ወልዋሎ ዓ/ዩ ከሱዳኑ ሂላል አልሳሕል ጋር የሚያደርገውን የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች በዛሬው ዕለት ታውቀዋል። ጨዋታውን ለመምራት የተመደቡ ዩጋንዳውያን ዳኞች ሲሆኑ ዱላ ጆሽዋ ዋና ዳኛ፤ ዊልያም ኦሎያ አራተኛ ዳኛ እንዲሁም ሮናልድ ካቴንያ እና አሽራፍ ማጎላን ደሞ ረዳት ዳኞች ሆነው መመረጣቸው ታውቋል።

ወልዋሎ ከሱዳኑ ሂላል አል ሳህል ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ዓርብ ነሐሴ 29 ኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ላይ ሲደረግ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ቅዳሜ መስከረም 2 በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚያከናውን ይታወቃል።