ሲዳማ ቡና ከ ኤግሎን የሚያደርጉትን የመልስ ጨዋታ የሚመሩ የጨዋታ አመራሮች ታውቀዋል

ኢትዮጵያን በመወከል በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ከቻዱ ኤጌሎን ጋር ያለ ግብ ተለያይቶ የተመለሰው ሲዳማ ቡና የመልሱን ጨዋታ በዕለተ እሁድ በድሬዳዋ ስታዲየም የሚያደርግ ሲሆን ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞችም ታውቀዋል።
በዚህም መሠረት አራት የቦትስዋና ዜግነት ያላቸው ዳኞች ማለትም ጋኦላኦልዌ ካቤትስዌ ኬቶቦጊሌ በዋና ዳኝነት ፤ ሙኬትሲ ቤንጃሚን ማንካንኩ እና ጋሴላሜ ቲሎሎ ሞሎፌ በረዳት ዳኝነት ፤ ታባንግ ኬትሻቢሌ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት ሲመደቡ ደቡብ ሱዳናዊው ማኩር ማጆክ ካራዎም ማጆክ ማቢል ደግሞ የጨዋታው ኮሚሽነር ናቸው።

