ወሳኙ ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል

ወሳኙ ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል

ወልዋሎ ከቀናት በኋላ የሚያደርገው የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ የመልስ ጨዋታ የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኝ ክለቡ አስታውቋል

ወልዋሎ እና የሱዳኑ ክለብ ሂላል አል ሳሕል መስከረም 2 በድሬዳዋ ስታድየም የሚያደርጉት የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ የመልስ ጨዋታ በይፋዊ የወልዋሎ ገፅ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ክለቡ አስታውቋል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊ ውድድር በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ወልዋሎ በመጀመሪያው ጨዋታ በጠባብ ውጤት ሁለት ለአንድ ሽንፈት ማስተናገዱ የሚታወስ ሲሆን በመልሱ ጨዋታ ድል አድርጎ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍም ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።