የአስቻለው ታመነ ማረፊያው ታውቋል

የአስቻለው ታመነ ማረፊያው ታውቋል

ባለፉት ዓመታት ከታዩ ምርጥ ተከላካዮች መካከል አንዱ የሆነው አስቻለው ታመነ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል

ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት የመራው እና ከዚህ ቀድም በዲላ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ፋሲል ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው ተከላካይ አስቻለው ታመነ በቅርቡ ቀሪ የአንድ ዓመት እየቀረው ከብርትካናማዎቹ ጋር በስምምነት መለያየቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የተጫዋቹ ቀጣይ ማረፊያ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለመሆን መቃረቡን ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። ሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ኮከብ ተጫዋችነትን ክብር ያገኘው አስቻለው በአሁኑ ሰዓት ወደ ክለቡ የሚያደርገው ዝውውር በማገባደድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የህክምና ምርመራውንም አድርጓል፤ በተጨማሪም የአንድ ዓመት ውል ለመፈራረም መስማመቱንም አውቀናል።