አማካዩ ከነገው ጨዋታ ውጭ ሆነ

አማካዩ ከነገው ጨዋታ ውጭ ሆነ

በረከት ወልዴ ከወሳኙ ጨዋታ ውጭ መሆኑ ተረጋገጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት 10 ሰዓት ከሴኔጋል ጋር የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን እንደሚያከናውን ይታወሳል። ዋልያዎቹ ለዚህ ጨዋታ ይረዳቸው ዘንድ በባሕር ዳር ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዳቸውን ያከናወኑ ሲሆን አማካዩ በረከት ወልዴም በዛሬው ልምምድ አልተሳተፈም። በአሁኑ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ የሚገኙት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌም በዛሬው ልምምድ መሳተፍ ያልቻለው በረከት ወልዴ ከነገው ወሳኝ ጨዋታ ውጭ መሆኑ ገልፀዋል።