አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች ቅጣት ተላለፈባቸው

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች ቅጣት ተላለፈባቸው

የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጠንከር ያለ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

በ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ በሜዳው ሀላባ ስታዲየም በባህር ዳር ከተማ 3ለ1 መሸነፉ ይታወሳል።

በዚህ ጨዋታ ላይ 90+4ኛው ደቂቃ ላይ በተፈጠሩ ሰጣ ገባዎች የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳደብ እና በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣት ለፈጸሙት ጥፋት 6 ጨዋታዎች እንዲሁም አሰልጣኙ ቀይ ካርድ ካገኙ በኋላ ከአራተኛ ዳኛው ጋር ለፀብ በመጋበዛቸው እና ጨዋታውን ለ3 ደቂቃዎች በማዘግየታቸው 4 ጨዋታዎች በድምሩ 10 ጨዋታዎች እንዲቀጡ በተጨማሪም በድምሩ 10ሺህ ብር እንዲከፍሉ ውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ መወሰኑ ታውቋል።

* ከዚሁ ጋር በተያያዘ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የጨዋታው 90+4ኛ ደቂቃ ላይ የጨዋታውን ሁለተኛ ረዳት ዳኛ በድንጋይ በመወርወር መምታታቸውን የሚገልጽ ሪፖርት የቀረበባቸው ሲሆን የ50ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።