አዲስ አበባ ከተማ ከ ጅማ አባ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ተጠናቀቀ፡ አዲስ አበባ ከተማ 0-1 ጅማ አባ ቡና
8′ አሜ መሃመድ


ተጠናቀቀ ፡ ሙገር ሲሚንቶ 0-1 ፋሲል ከተማ
4′ አቡበከር ደሳለኝ


ተጠናቀቀ
ጨዋታው በጅማ አባ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ባለመሸነፍ ጉዞውም ቀጥሏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አባ ቡና
84′ ኪዳኔ አሰፋ ወጥቶ ዳንኤል ስለሺ ገብቷል፡፡

81′ ፍቃዱ አለሙ በድጋሚ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አባ ቡና
79′ ቢንያም ሃይሌ ወጥቶ ሳሙኤል ብርሃኑ ገብቷል፡፡

78′ ፍቃዱ አበበ በግንባሩ የገጨው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

* አአ ከተማዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስዱም የአባ ቡናን ጠንካራ የተከላካይ መስመር ሰብረው መግባት አልቻሉም፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አአ
75′ ዳዊት ማሞ ወጥቶ ሚካኤል በደኘ፡ነ ገብቷል፡፡

71′ ፍቃዱ አለሙ በግቡ አቅራቢያ የተመቻቸ ኳስ አግኝቶ የመታውን ኳስ ሂደር ተደርቦ አውጥቶበታል፡፡

61′ ዘሪሁን የመታውን ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ሙላት በቀላሉ ይዞታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አአ
59′ ሃይሌ እሸቱ ወጥቶ ኢሳያስ ታደሰገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
49′ ሂደር ሙስጣፋ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ – አባ ቡና
ፓትሪክ ኑምባሲ ወጥቶ አብርሃም አለሙ ገብቷል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በጅማ አባ ቡና መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ ሙሃጅር መኪ የመታው ቅጣት ምት በግቁ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

44′ ጨዋታው በጉሽሚያ የተሞላ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ በርካታ ጥፋቶቸችም እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
30′
ሃይለየሱስ መልካ ወጥቶ ሙሃጅር መኪ ገብቷል፡፡

28′ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ቢንያም ሃይሌ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

20′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

ጎልልል!!!! ጅማ አባ ቡና
8′ አሜ መሃመድ ጅማ አባ ቡናን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

2′ አሜ መሃመድ በግራ አግሩ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በጅማ አባ ቡና አማካኝነት ተጀመረ::


የአዲስ አበባ ከተማ አሰላለፍ

1 ተክለማርያም ሻንቆ

2 እንየው ካሳሁን – 17 ዳንኤል አባተ – 21 ሚልዮን ብሬ – 7 ምንያምር ጴጥሮስ –

8 ዮናታን ብርሃኔ – 4 ዘሪሁን ካሳሁን – 6 ሃይለየሱስ መልካ – 11 ዳዊት ማሞ

9 ሃይሌ እሸቱ – 24 ፍቃዱ አለሙ


የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ

1 ሙላት አለማየሁ

3 ተመስገን ደረሰ – 11 ሂደር ሙስጠፋ – 4 በሃይሉ በለጠ – 5 ጀሚል ያዕቆብ

16 ኪዳኔ አሰፋ – 25 ቴዎድሮስ ገ/ፃድቅ – 17 ቢንያም ሃይሌ – 14 ቢንያም ተፈራ

7 ፓትሪክ ኑምባሲ – 13 አሜ መሃመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *