ፕሪሚየር ሊግ ፡ ኤሌክትሪክ እና ንግድ ባንክ ድል ቀንቷቸዋል

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1 ወር መቋረጥ በኋላ ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸንፈዋል፡፡

በ9፡00 ሀዲያ ሆሳእናን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንገድ ባንክ 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ የንግድ ባንክን ወሳኝ የማሸነፍያ ግብ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው ከመረብ ያሳረፈው የመስመር ተከላካዩ አንተነህ ገብረክርስቶስ ነው፡፡ በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ቶክ ጀምስ ከእንቅስቃሴ ውጪ በእጁ በመማታቱ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ የተወገደ ሲሆን ወጣቱ ቢንያም በላይ ተቀይሮ በመግባት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመርያ ጨዋታውን አድርጓል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ንግድ ባንክ በ10 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዲያ ሆሳዕና በ4 ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል፡፡

በ11፡30 ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው ኤሌክትሪክ 2-1 አሸንፏል፡፡ ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ሀዋሳዎች ሲሆኑ በ25ኛው ደቂቃ ግቧን ያስቆጠረው ታፈሰ ሰለሞን ነበር፡፡ ከ6 ደቂዎች በኋላ በ31ኛው ደቂቃ አሳልፈው መኮንን ቀዮቹን አቻ አድርጎ ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ ከእረፍት መልስ በ53ኛው ደቂቃ ሴራሊዮናዊው ተከላካይ ሲሴ ሃሰን 2ኛ ግብ አስቆጥሮ ኤሌክትሪክ 3 ነጥብ እንዲሰበስብ አድርጓል፡፡ ድሉን ተከትሎ ኤሌክትሪክ በ10 ነጥብ ወደ 8ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ተሸናፊው ሀዋሳ ከተማ በ6 ነጥቦች 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሊጉ ነገ እና ረቡእ በሚደረጉ ጨዋታዎች ሲቀጥል ነገ በ9፡00 ደደቢት ከ አርባምንጭ በ11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ድቻ ይጫወታሉ፡፡ አበበ ቢቂላ ላይ ደግሞ በ10፡00 ኢትዮጵያ ቡና ዳሽን ቢራን ያስተናግዳል፡፡ ረቡዕ አዳማ ከተማ ሲዳማ ቡናን ሲያስተናግድ በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያ ከ ድሬዳዋ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

Unsssssstitled

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *