ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ንግድ ባንክ ተጨማሪ ዝውውርን ፈፅሟል

ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ንግድ ባንክ ተጨማሪ ዝውውርን ፈፅሟል

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ተካፋዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨማሪ ተጫዋች ሲያስፈርም የአንድ ነባር ውልንም አድሷል።

የስምንት ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው እና በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሚካፈለው በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ምርቃት ፈለቀን ፣ እፀገነት ግርማ ፣ ቤቴልሄም ግዛቸው እና እሙሽ ዳንኤል በማስፈርም የግብ ዘቧን ታሪኳ በርገናን ኮንትራት ደግሞ ያደሰ ሲሆን ዛሬ ደግሞ አንድ አዲስ እና አንድ ነባርን አስፈርሟል።

በአርባምንጭ ከተማ በመጫወት ከኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ጋር የተዋወቀችው እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ የነበረችው የመሐል ተከላካዩዋ ትዕግሥት አዳነ አዲሷ የቡድኑ ፈራሚ ስትሆን ከሀዋሳ ከተማ ንግድ ባንክን በመቀላቀል ዓመቱን ያሳለፈችው ተከላካዩዋ ቅድስት ዘለቀ ደግሞ ኮንትራቷን ለተጨማሪ ዓመት አራዝማለች።