“በዚህ ጉዞ ፌዴሬሽኑ የሚያወጣው አምስት ሳንቲም ወጪ የለም።” አቶ ባሕሩ ጥላሁን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመጓዝ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ዋልያዎቹ ነገ ማምሻውን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በማቅናት ሐምሌ 26 ለሚያደርገት ጨዋታ አስመልክቶ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል አስተዳደራዊ እና ቴክኒካዊ ዝግጅት በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል። በዚህ ወቅት ታዲያ የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የቡድኑ ጉዞ ዙርያ የሚወጣውን ወጪ እና ገቢውን አስመልክቶ ተከታዩን ብለዋል።
“ወደ አሜሪካ በመጓዙ የ25 ሺህ ዶላር ያገኛል። ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለ 50ሺህ ዶላር ሽልማትን ያገኛል። ብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ አሜሪካ በሚጓዝበት ወቅት የቡድኑ አባላት የአውሮፕላን ፣ የሆቴል እና ሌሎች አጠቃላይ ወጪዎችን ዲሲ ዩናይትድ የሚሸፍን ይሆናል። ስለዚህ በዚህ ጉዞ ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያወጣው አምስት ሳንቲም ወጪ የለም።”