መቻል የሁለገቡን ተጫዋች ውል አራዘመ

መቻል የሁለገቡን ተጫዋች ውል አራዘመ

ከሰሞኑን በዝውውር ገበያው በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው መቻል የሁለገቡን ተጫዋች ውል ማራዘሙ ታውቋል።

በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው መቻል ያለፉትን አራት ቀናት ወሳኝ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኝ ሲሆን ከአዲሶች በተጨማሪ የግብ ጠባቂው ውብሸት ጭላሎ ውል ለተጨማሪ ዓመታት ማራዘሙን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሠረት ደግሞ ግሩም ሀጎስ ውሉን አራዝሟል።

ያለፉትን አራት አመታት በመቻል ቤት ቆይታ ያደረገው ግሩም በመስመር ተከላካይነት፣ በመስመር አጥቂነት እንዲሁም በአማካይ መስመር ተጫዋችነት ቡድኑን እያገለገለ እንደሚገኝ ይታወቃል።