ሽመልስ በቀለ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተቃርቧል

ሽመልስ በቀለ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተቃርቧል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ስኬታማ ዓመታቶችን ያሳለፈው ሽመልስ በቀለ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ መቃረቡን አውቀናል።

የእግርኳስ ህይወቱን በኮረም ሜዳ የጀመረው አማካዩ ሽመልስ በቀለ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ በክለብ ደረጃ በሀዋሳ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ በማስከተል ከሀገር ውጭ ለሱዳኑ ኤል ሜሪክ እና አል ኢትሀድ እንዲሁም ወደ ግብፅ በማቅናት ለግብፆቹ ክለብ ፔትሮጀት (አምበል ) ፣ ኤል ጉና፣ ምስር አልመካሳ እና ኤንፒ በመጫወት የፕሮፌሽናል የእግርኳስ ህይወቱን ከመራ ከአስር ዓመታት በኋላ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ለመቻል ሁለት ዓመታት መጫወቱ ይታወሳል።

ከመቻል ጋር የውል ዘመኑ መጠናቀቁን ተከትሎ ሽመልስን ለማስፈረም ከባህር ዳር ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ጋር ድርድር ያደረገ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ የሽመልስ ማረፊያ ሀዋሳ ከተማ ለመሆን መቃረቡን አውቀናል።