የጦና ንቦቹ የተከላካያቸውን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል

የጦና ንቦቹ የተከላካያቸውን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሀገራችንን የሚወክለው ወላይታ ድቻ ተከላካዩን ለተጨማሪ ዓመት በስብስቡ ለማቆየት ስምምነት ፈፅሟል

አሠልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን ለመሾም እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ከ2018 የሊጉ ውድድር ባለፈ ከፊቱ ለሚጠብቀው አህጉራዊ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፍልሚያ ከሰሞኑን ወደ ዝውውሩ የገባ ሲሆን በተለይ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል ማደስ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ተከላካዩ መልካሙ ቦጋለ ለተጨማሪ ዓመት በጦና ንቦቹ ማሊያ ለመቆየት ተስማምቷል። ከወላይታ ታዳጊ ቡድን በማደግ ያለፉትን አምስት ዓመታት በዋናው ቡድን ራሱን ያሳየው መልካሙ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጉዳት ምክንያት ከ717 ደቂቃዎች በላይ ተሳትፎ ማድረግ አለመቻሉ ይታወቃል።

ወላይታ ድቻ ከተከላካዩ መልካሙ በተጨማሪ የግብ ዘቡ አብነት ይሳቅን ውልም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘሙ ይፋ ሆኗል።