ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሦስት ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሦስት ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል

የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሦስት ነባር ተጫዋቾቻውን ለማቆየት ተስማምተዋል።

አስቀድመው የሀብታሙ ሸዋለም፣ የአሸናፊ ጥሩነህ እና በፍቃዱ አስረሳህኝ ውል ያራዘመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሁንም ውል በማራዘም ስራዎች ተጠምዶ የሦስት ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል።

ውሉን ያራዘመው የመጀመርያው ተጫዋች የ2016 የከፍተኛ ሊጉ ኮከብ ግብጠባቂ የነበረው የግብ ዘቡ አሸብር ተስፋዬ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በተጠባባቂነት ቢያሳልፍም ከቡድኑ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል። ሌላኛው ውሉን ያራዘመው ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ያገለገለው የቡድኑ ሦስተኛ ግብ ጠባቂ ወጣቱ ኪሩቤል ሀይሌ ነው። እንዲሁም ከታዳጊ ቡድኑ አንስቶ አሁንም ድረስ ለዋናው ቡድን እየተጫወተ ያለው በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈው ወጣቱ አማካይ ሙከረብ ረሺድ ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ ለመቆየት ውሉን ያራዘመ ተጫዋች ነው።

እስካሁን የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ከማራዘም ውጭ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው ያልቀላቀሉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በቅርቡ ወደ ዝውውሩ እንደሚገቡ ይጠበቃል።