የቀኝ መስመር ተከላካዩ በረከት ወልደዮሐንስ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል።
ውላቸው የታጠናቀቁ የስድስት ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩን በረከት ወልደዮሐንስ አስፈርመዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በነብሮቹ መለያ በ29 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 2520 ደቂቃዎችን በሜዳ ላይ ለቡድኑ አገልግሎት የሰጠው ሁለገቡ ተከላካይ በረከት ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ፣ አርባምንጭ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን አሁን መዳረሻውን ለአንድ ዓመት ኢትዮ ኤሌክትሪክን አድርጓል።
