የጣና ሞገዶቹ የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዝመዋል

የጣና ሞገዶቹ የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዝመዋል

ባህር ዳር ከተማ የባለ ልምዱን አማካይ እና የታዳጊውን የመስመር ተጫዋች ውል አራዝሟል።

ዮሐንስ ደረጄን ከድሬዳዋ ፣ ብሩክ ሰሙ እና ማንያዘዋል ካሳን ደግሞ ከከፍተኛ ሊጉ ከቤንች ማጂ ቡና ያስፈረሙት የጣና ሞገዶቹ ከመሳይ አገኘሁ ቀጥሎ የተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል።

ውሉን ለማራዘም የተስማማው የመጀመሪያው ተጫዋች ፍቅረሚካኤል ዓለሙ (አቢ) ሲሆን ከከፍተኛ ሊግ ጀምሮ በጣና ሞገዶቹ ቤት ትልቅ ግልጋሎት በመስጠት እና ባለፉት ሰባት ዓመታት የባህር ዳር ከተማ የፕሪሚየር ሊግ ቆይታም ከቡድኑ ጋር መዝለቅ የቻለው አማካዩ ለተጨማሪ ዓመት የሚቆይበትን ውል አድሷል።

ሌላኛው ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ደግሞ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ታዳጊው የመስመር ተጫዋች አምሳሉ ሳለ ነው። ከሁለት ዓመታት በፊት በጣና ሞገዶቹ ማልያ ከፕሪሚየር ሊጉ ጋር የተዋወቀው ተጫዋቹ ለተጨማሪ ዓመት በባህር ዳር ከተማ ለመቆየት የተስማማ ሌላኛው ተጫዋች ሆኗል።