የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ እያደረጉ የሚገኙት መድኖች አራተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።
የአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ ኢትዮጵያ መድኖች ወደ ዝውውሩ በይፋ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም እና ሦስት አዳዲሰ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የግብ ዘቡን በቃሉ አዱኛን ማስፈረማቸው ታውቋል።
ግብ በጠባቂው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊግ ለሶሎዳ አዳዋ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ከዚህ ቀድም ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በአዳማ ከተማ የግብ ጠባቂ ህይወቱን ያሳለፈ ሲሆን አሁን ማረፊያውን ለሁለት ዓመት ኢትዮጵያ መድን አድርጓል።