የተጫዋቾቻቸውን ውል በማደስ የተጠመዱት የጣና ሞገዶቹ የመስመር ተከላካያቸውን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል።
ዮሐንስ ደረጄ፣ ብሩክ ሰሙ እና ማንያዘዋል ካሳን አስፈርመው የመሳይ አገኘሁ ፣ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ እና አምሳሉ ሳለን ውል ያደሱት ባህር ዳር ከተማዎች አሁን ደግሞ የመስመር ተከላካያቸውን ግርማ ዲሳሳ ውል አድሰዋል።
ባህር ዳር ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድግ የአንበሳውን ድርሻ የወሰደው እና ረዘም ያሉ ዓመታት በባህር ዳር ከተማ በማሳለፍ በመሃል ወደ መቻል አምርቶ በድጋሚ ወደ ባህር ዳር ተመልሶ መጫወት የቻለው የመስመር ተጫዋቹ ግርማ ዲሳሳ በባህር ዳር ከተማ ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።
