በርከት ያሉ ተጫዋቾቻቸውን ውል እያደሱ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ የተከላካያቸውን ውል አድሰዋል።
በወጣት ተጫዋቾች ቡድናቸውን እያዋቀሩ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ከዚህ ቀደም ዮሐንስ ደረጄ፣ ብሩክ ሰሙ እና ማንያዘዋል ካሳን በማስፈረም የመሳይ አገኘሁ ፣ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ፣ አምሳሉ ሳለ እና ግርማ ዲሳሳን ውል እንዳደሱ የዘገብን ሲሆን አሁን ደግሞ የመሃል ተከላካያቸውን ክንዱ ባየልኝ ውል አድሰዋል።
የእግርኳስ ጅማሮውን በባህር ዳር ከተማ ታዳጊ ቡድን ያደረገው እና በከፍተኛ ሊጉ ለሚወዳደረው ባቱ ከተማ ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ወደ አሳዳጊ ክለቡ በመመለስ መጫወት የቻለ ሲሆን በሞገደኞቹ ቤት ለመቆየት ውሉን አድሷል።