የጣና ሞገዶቹ የቪድዮ ትንተና ባለሞያ ዋልያዎቹን ተቀላቀለ።
ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያደርጋቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ ባለሞያ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ቀደም ብለው በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ምትክ አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞን በምክትል አሰልጣኝነት መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ባለፉት ዓመታት በባህርዳር ከተማ በቪድዮ ትንተና ባለሞያነት ሲሰራ የቆየው መብራቱ ሀብቱን ወደ አሰልጣኞች ቡድናቸው አካተዋል።
ባለሙያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቪድዮ ትንተና ኮርስ በመውሰድ የምስክር ወረቀት እንዳለው ይታወቃል።