ቡድናቸውን በወጣት ተጫዋቾች እያደራጁ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ ወጣቱን አማካይ ወደ ስብስባቸው ሲቀላቅሉ የግብ ጠባቂያቸውን ውል አድሰዋል።
ከዚህ ቀደም ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ተጠምደው የቆዩት ባህር ዳር ከተማዎች አሁን ደግሞ ወጣቱን አማካይ አናንያ ጌታቸውን የግላቸው ማድረግ ችለዋል።
መነሻውን በባህር ዳር ፕሮጀክት አድርጎ በአውስኮድ ታዳጊ ቡድን፣ ጅማ አባጅፋር እና ያለፈውን አመት በመድን ቤት ማሳለፍ የቻለው አናንያ በቀጣይ በውሃ ሰማያዊው ማልያ የምንመለከተው ሌላኛው ተጫዋች ሲሆን በተጨማሪ መነሻውን ከአውስኮድ ያደረገው ግብጠባቂው ይገርማል መኳንንት ሌላኛው ውሉን ያደሰ ተጫዋች ነው።