የኢትዮጵያ ዋንጫን አስመልክቶ ሲዳማ ቡና አዲስ ውሳኔ አሳልፏል።
የ2017 የውድድር ዘመን በተካሄደው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን በማሸነፍ ዋንጫውን ከፍ አድርጎ ማንሳቱ ይታወሳል። ሆኖም ሲዳማ ቡና ተገቢነት የሌለው ተጫዋች በመጠቀሙ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውጤቱን በፎርፌ በመሰረዝ ዋንጫው ለወላይታ ድቻ እንዲመለስ እና የጦና ንቦቹ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፉ መወሰኑም አይዘነጋም።
ሲዳማ ጉዳዩን ወደ ካስ (የእግርኳሱ ገላጋይ ፍርድ ቤት) ይዞት ቢሄድም ጥያቄው ውድቅ ተደርጎበትም ነበር። ከዚህ በኋላ የሚጠበቀው ሲዳማ ቡና የወሰደውን ዋንጫ እንዲመልስ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሰጠው መመርያ መሠረት ሲዳማ ቡና ዋንጫውን በክብር ለመመለስ ተስማምቷል።
በዚህም ዛሬ የሲዳማ ቡና ተወካዮች ዋንጫውን በመያዝ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት በመገኘት በክብር እንደሚመልሱ ዝግጅት ክፍላችን አውቃለች።