ሦስቱም ክለቦች  የሚጠበቅባቸው የቅጣት ገንዘብ ፈፅመዋል

ሦስቱም ክለቦች የሚጠበቅባቸው የቅጣት ገንዘብ ፈፅመዋል

የሊጉ ሦስት ክለቦች ለፈፀሙት የህግ ጥሰት የሚጠበቅባቸውን የቅጣት ክፍያ መፈፀማቸው ታውቋል።


የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር የፋይናንስ አጣሪ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የፋይናንስ ደንብ በጣሱ 3 ክለቦች እና በ14 ተጨዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ይታወሳል። ይህን ተከትሎ መቻል ለ7 ተጫዋቾች ቅድመ ክፍያ(በሶስተኛ ወገን) በመክፈሉ ብር 21,000,000 እንዲቀጣ፣ ሲዳማ ቡና ለ6 ተጫዋቾች ቅድመ ክፍያ(በሶስተኛ ወገን) በመክፈሉ ክለቡ በሰጣቸው 6 ተጫዋቾች ብር 18,000,000 እንዲከፍል እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ አንድ ተጫዋች ቅደመ ክፍያ (በሶስተኛ ወገን) በመክፈሉ ብር 3,000,000 እንዲቀጣ መወሰኑ አይዘነጋም።

ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ አስቀድመው የቅጣት ክፍያውን ከፈፀሙት መቻል እና ሀዋሳ ከተማን በተጨማሪ ዛሬ ክፍያውን የፈፀመው ሲዳማ ቡና ጨምሮ ሦስቱም ክለቦች የቅጣት ገንዘባቸውን መክፈላቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም የሊጉ አክስዮን ማህበር ከሦስቱ ክለቦች በቅጣት 42,000,000 ብር ገቢ አግኝቷል።