የሁለት ነባር ተጫዋቾን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ የገቡት ሲዳማ ቡናዎች ፊታቸውን ወደ ከፍተኛ ሊግ አዙረዋል።
ከሰዓታት በፊት የግቡ ዘቡን እና የመስመር ተካላካዩን ውል ማራዘም የቻሉት ሲዳማዎች ሁለት ተከላካዮችን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ቡድናቸው ለማቀላቀል ስምምነት ፈፅመዋል።
የመጀመሪያው ፈራሚ ተከላካዩ ሞገስ ቱሚቻ ሲሆን የእግር ኳስ ህይወቱን በሀዋሳ ከተማ ጅማሮውን ካደረገ በኋላ በወልዲያ ከተማ፣ ጋሞ ጨንቻ እንዲሁም በዘንድሮው ወድድር ዘመን ደሴ ከተማ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ በሲዳማ ቡና ቤት ለሁለት አመት ለመቆየት ተስማምቷል።
ሌላኛው ፈራሚ የግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ማቲዮስ ነው። ከኢትዮጵያ መድን ተስፋ ቡድን ከተገኘ በኋላ ለቡታጅራ ከተማ እና ዘንድሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታ አድርጎ በክረምቱ ዝውውሩ መስኮት ሲዳማ ቡና ለመግባት የተሰማማ ሲሆን ለሁለት አመት ለመቆየት ስምምነት ላይ ደርሷል።