በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ጠንካራ ተሳታፊ የነበሩት መቻሎች ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።
መቻሎች ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በሊጉ ደካማ የሆነ እንቅቃሴን በማድረግ በአመቱ በአጠቃላይ ካደረጓቸው 34 ጨዋታዎች በፋይናንስ ጥሰቱ የተቀነሱትን ነጥቦች ጨምሮ በአጠቃላይ 33 ነጥቦችን በመሰብሰብ ወራጅ ቀጠናው ውስጥ በመሆን 15ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው።
በውድድር አመቱ ደስተኛ ያልነበሩት የመቻል አመራሮች አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በማሰናበት ባሳለፍነው ዓመት በሐዋሳ ቤት ድንቅ ጊዜ ያሳለፈውን ሙሉጌታ ምህረት ዋና አሰልጣኝ በማድረግ ሹመዋል።
በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመሩት መቻሎች ባሳለፍነው የውድድር ዓመት የታዩ ድክመቶች እና ክፍተቶችን ለማረም ብሎም ቡድኑን ለ2018 የውድድር ዓመት ጠንካራ እና ተፎካካሪ ለማድረግ በዝውውር ገበያው በትኩረት በመሳተፍ ስብስቡን እያጠናከረ የሚገኘው መቻል ቸርነት ጉግሳ፣ የአብስራ ተስፋዬ፣ፈቱዲን ጀማል ፣ መሐመድ አበራ፣ ብሩክ ማርቆስ እና ቻላቸው መንበሩን ማስፈረም የቻሉ ሲሆን ሌሎች የዝውውር ጉዳዮችን እየሰሩ ዝግጅታቸውን በደብረ ዘይት ከተማ ማድረግ ጀምረዋል።