ፈረሰኞቹ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

ፈረሰኞቹ ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የቅድመ ውድድር ዝግጅት መቼ እንደሚጀምሩ አውቀናል።


ተከታታይነት ያልታየበት የውጤት ጉዞ እያስመለከቱን የውድድር ዘመኑን ያጠናቀቁት  ቅዱስ ጊዮርጊሶች ተሻሽሎ በቀረበው የደረጃ ሠንጠረዥ ስድስተኛ ሆነው መጨረሳቸው ይታወሳል። ለከርሞ ራሳቸውን ለማጠናከር ከከፍተኛ ሊጉ አዲሱ አቱላ፣ መሳፍንት ጳውሎስ እና ቡአይ ኩዌትን ሲያመጡ ከሊጉ ደግሞ ጥዑመልሳን ኃይለሚካኤል እና አበባየሁ ዮሐንስን አስፈርመዋል። ውላቸው ተጠናቆ የነበረው ግብ ጠባቂው ተመስገን ዮሐንስ፣ አብርሃም ጌታቸው፣ ተገኑ ተሾመ እና ሻይዱ ሙስጠፋን ማቆየት የቻሉት ፈረሰኞቹ ሳይጠበቅ አቤል ያለውን ዳግም ወደ ክለባቸው መመለስ ችለዋል።

በቀጣዮቹም ቀናትም ዝውውሮችን እንደሚፈፅሙ የሚጠበቁት ፈረሰኞቹ አሁን ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን መቼ እንደሚጀምሩ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች ።

እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ቢሸፍቱ በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ አካዳሚ ሰኞ የሚሰባሰቡ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ዝግጅት ለመጀመር መታሰቡን አውቀናል።