የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ከፊፋ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ታውቋል።
የካፍ ስራ አስፈፃሚ አባል በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በፊፋ የፀረ ዘረኝነት እና ፀረ አድልዎ ( “Anti-Racism & Anti – Discrimination“) ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል።
ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በዚህ ጉዳይ ላይ በአፍሪካም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥረት አድርገው ትልቅ ክብር እንዳገኙበት ይታወሳል።