ወልዋሎ የመሃል ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማማ

ወልዋሎ የመሃል ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማማ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሸገር ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

በዝውውር መስኮቱ በርከት ያሉ ተጫዋቾች በማስፈረም እና የነባሮችን ውል በማራዘም ላይ ያሉትና በትናንትናው ዕለት ዩጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ ጆኤል ሙታኩብዋ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ባለፈው ዓመት በሸገር ከተማ ቆይታ የነበረውን የመሀል ተከላካዩ ኪም ላም ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በ2017 የውድድር ዓመት ሸገር ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ ትልቅ አስተዋፆ ካደረጉ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ተጫዋቹ ከመቻል ወጣት ቡድን ከወጣ በኋላ ባለፉት ዓመታት በባቱ ከተማ፣ ንብ እንዲሁም ሸገር ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ በክረምቱ የዝውውር መስኮት  በርካታ ዝውውሮች ፈፅመው ለ2018 የውድድር ዓመት በመዘጋጀት ላይ ለሚገኙት ወልዋሎዎች ፊርማውን ለማኖር ከስምምነት ደርሷል።