መቐለ 70 እንደርታ የመስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

መቐለ 70 እንደርታ የመስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአዞዎቹ ጋር ቆይታ የነበረው ተጫዋች ምዓም አናብስትን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

በዝውውር መስኮቱ  ሱሌይማን ሐሚድ፣ መሐሪ አመሀ፣ አብዲ ዋበላ፣ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ፣ ብርሃኑ አዳሙ፣ ጊት ጋትኮች፣ ፍፁም ዓለሙ፣ ፍሬዘር ካሳ እና ኪቲካ ጅማን ለማስፈረም ተስማምተው የበርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ምዓም አናብስት አሁን ደግሞ ባለፈው ዓመት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረው የፊት መስመር ተጫዋቹ በፍቅር ግዛውን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአርባ ምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረው እና በውድድር ዓመቱ በ21 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1538′ ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል ሦስት ግቦች ያስቆጠረው የመስመር ተጫዋቹ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከተስማማ በኋላ ስብስቡን ተቀላቅሎ ልምምድ ጀምሯል። ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን ተገኝቶ በቡድኑ ከ 17 ዓመት በታች እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ከተጫወተ በኋላ ባለፉት ዓመታት በእናት ክለቡ ሲዳማ ቡናና አርባ ምንጭ ከተማ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና በተመራው ከ17 ዓመት ብሔራዊ ቡድንም አባል እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ለሚሰለጥነው መቐለ 70 እንደርታ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።