መቻል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፍጻሜ ደርሰዋል

መቻል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፍጻሜ ደርሰዋል

በአዲስ አበባ ከተማ ሕዳሴ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ጦሩ እና ፈረሰኞቹ ተጋጣሚያቸውን ማሸነፍ ችለዋል።

መቻልን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀኑ 7:00 ሲል ያገናኘው ጨዋታ ቀዳሚው ነበር። በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረት የሚመሩት መቻሎች ኮሊን ኮፊ ከዕረፍት በፊት ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ታግዘው ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ሌላኛው ተጠባቂ በነበረው ጨዋታ በሀገራችን ትልቁ ደርቢ የሆነው አዲስ አበባ ደርቢ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ተደርጓል።

ብዛት ባላቸው የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች ህብረ ዜማ ታጅቦ የተጀመረው ይህ ጨዋታ በግብ ማግባቱ ዘንድ ኢትዮጵያ ቡናዎች በ1’ኛው ደቂቃ በአቡበከር አዳሙ እና በ28’ኛው ደቂቃ በፍቃዱ ዓለማየሁ ግብ 2-0 መምራት ችለው የነበረ ቢሆንም ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበቢኒያም ፍቅሩ ሁለት ግቦች እንዲሁም የቡናው ፉዓድ ኢብራሂም በራሱ ላይ ባስቆጠረው ግብ ታግዘው ከመመራት ተነስተው 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 9 ሰዓት መቻል ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፍጻሜ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደርጋሉ። አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 9 ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና ለደረጃ ይጫወታሉ።