መቐለ 70 እንደርታ ሁለገቡን ተጫዋች ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

መቐለ 70 እንደርታ ሁለገቡን ተጫዋች ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ባለፈው ዓመት ከዐፄዎቹ ጋር ቆይታ የነበረው ተጫዋች ምዓም አናብስትን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

በዝውውር መስኮቱ ሱሌይማን ሐሚድ፣ መሐሪ አመሀ፣ አብዲ ዋበላ፣ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ፣ ብርሃኑ አዳሙ፣ ጊት ጋትኮች፣ ፍፁም ዓለሙ፣ ፍሬዘር ካሳ እና ኪቲካ ጅማን ለማስፈረም ተስማምተው የበርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ምዓም አናብስት አሁን ደግሞ ባለፈው ዓመት በፋሲል ከነማ ቆይታ የነበረው በመስመር አጥቂነት እንዲሁም በአማካይ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለውን አፍቅሮተ ሰለሞንን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በተጠናቀቀው ዓመት በፋሲል ከነማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ከደደቢት ታዳጊ ቡድን ከወጣ በኋላ በ2011 በፕሪምየር ሊጉ በ2012 ደግሞ በከፍተኛ ሊግ አሳዳጊ ክለቡን ያገለገለ ሲሆን ከዛ በኋላም በኢትዮጵያ መድን፣ ገላን ከተማ፣ ሀምበርቾ እንዲሁም በፋሲል ከነማ መጫወት ችላል፤ አሁን ደግሞ በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ወደ ሚመሩት ምዓም አናብስት ለማምራት መስማማቱን ተከትሎ ስብስቡን ተቀላቅሎ ልምምድ ጀምሯል።

* ቀደም ብለን “በፍቅር ግዛው መቐለ 70 እንደርታን ለመቀላቀል ተስማምቷል” በሚል በሰራነው ዜና ላይ ለተፈጠረው የመረጃ ስህተት አንባቢዎቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።