ምዓም አናብስት አጥቂውን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ምዓም አናብስት አጥቂውን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ባለፈው ዓመት በአዳማ ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

በመቀመጫ ከተማቸው መቐለ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ከቀናት በፊት ውድድሩ ወደ ሚደረግበት ድሬዳዋ ከተማ ያቀኑት እና በትናንትናው ዕለት አፍቅሮተ ሰለሞንን ለማስፈረም የተስማሙት በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ አጥቂው ስንታየሁ መንግሥቱን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

በ2017 የውድድር ዓመት በ 28 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2126′ ደቂቃዎችን ቡድኑን በማገልገል ስምንት ግቦችን ያስቆጠረው አጥቂው ከዚህ ቀደም በአሳዳጊ ክለቡ ወላይታ ድቻ፣ ባህር ዳር ከተማ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም በአዳማ ከተማ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ ስብስቡን በመቀላቀል ዛሬ ረፋድ ልምምድ ጀምሯል።