መቐለ 70 እንደርታ በተጫዋች ተገቢነት የነጥብ ቅነሳ ተደረገበት።
መቐለ 70 እንደርታ በ2017 የውድድር ዓመት በ36ኛው ሳምንት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዶ የአራት ጨዋታዎችን ቅጣት የተላለፈበት የመስመር ተከላካዩ ሱሌይማን ሐሚድን ማሰለፉን ተከትሎ ቅጣት ተላልፎበታል።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበውን የፎርፌ ውጤት ይገባኛል ጥያቄ መሰረት በውድድር እና ስነስርዓት ኮሚቴ ሲደረግ ከቆየው ማጣራት በኋላ ተጫዋቹ የመጨረሻውን ሳምንት ጨምሮ በ2ኛ ሳምንት ከመቻል፣ በ3ኛ ሳምንት ከድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም በ4ኛ ሳምንት ከሃዋሳ ከተማ ጋር በተደረጉ ጨዋታዎች መሰለፉን ተከትሎ ክለቡ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ሳምንት ያስመዘገባቸው ውጤቶች ተሰርዞ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን በተጨማሪም ሀያ ሺህ ብር አንዲከፍል እና የቡድን መሪው አቶ ተኽለ እያሱ ለ6 ወር እንዲታገዱ ተወስኗል።


