ከአሰልጣኝ አብይ ካሳሁን ጋር በስምምነት የተለያዩት ቡናማዎቹ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከጫፍ ደርሰዋል።
ከውጤት ማጣት ጋር ተያይዞ አጀማማራቸው ያላማረው ኢትዮጵያ ቡናዎች ከሰሞኑ ከቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አብይ ካሳሁን ጋር በስምምነት መለያየታቸው ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ሲንቀሳቀስ የቆየው የክለቡ ቦርድ ከተለያዩ አሰልጣኞች ጠርቶ ካወዳደረ በኋላ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ለመቅጠር መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ከዚህ ከቀደም ዳሽን ቢራ፣ ስሑል ሽረን ፣ ድሬደዋ ከተማን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን በሊጉ በማሰልጠን የሚታወቁ ሲሆን የጥቅማጥቅም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ድርድሮችን ካደረጉ በኋላ ቡድኑን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአሰልጣኝ ቅጥሩ የወረቀት ስራ አስኪጠናቀቅ ቡድኑ በቀጣይ ረቡዕ ከመቻል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በምክትሎቹ በኃይሉ አድማሱ እና ታፈሰ ተስፋዬ አማካይነት እንደሚመራ ለማወቅ ችለናል።

