ቢኒያም ፍቅሩ ወደ ሸገር ከተማ ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል

ቢኒያም ፍቅሩ ወደ ሸገር ከተማ ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል

ሸገር ከተማዎች የፊት መስመት ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማሙ።

ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ በኋላ ከቀናት በፊት ከፈረሰኞቹ ጋር በስምምነት የተለያየው የፊት መስመር ተጫዋቹ ቢኒያም ፍቅሩ ወደ ሸገር ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። ቀሪ የስድስት ወራት ውል እያለው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ከተለያየ በኋላ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ተጫዋቹ አሁን ወደ ሸገር ከተማ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል፤ የዝውውር መስኮቱ በይፋ ሲከፈትም ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።