የ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆነ።
በዛሬው ዕለት በግብፅ መዲና ካይሮ በሚገኘው የካፍ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው የ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ ውድድር የሴቶች እግር ኳስ የማጣሪያ ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው ዙር ከ ሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተደልድለዋል። ጨዋታውም ከመስከረም 24 እስከ ጥቅምት 3 2019 ዓ.ም ባሉት ቀናት እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለታል።

ይህ የማጣሪያ ውድድር በአምስት ዙሮች የሚካሄድ እና 35 ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳተፉበት ሲሆን ማጣሪያውን በበላይነት የሚያጠናቅቁ ሁለት ብሔራዊ ቡድኖችም በ2028 ሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ይሆናል።

