ሸገር ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኙን በዋናነት ሾመ

ሸገር ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኙን በዋናነት ሾመ

ሸገር ከተማዎች በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሲመሩ የቆዩትን አሰልጣኝ በዋናነት መቅጠራቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ሸገር ከተማ ከውጤት ማጣት ጋር ተያይዞ የቀድሞ ዋና አሰልጣኙን አሸናፊ በቀለን ካሰናበተ በኋላ ምክትል አሰልጣኙን ዶክተር ኢያሱ መርሐፅድቅን በጊዜያዊነት መሾሙ ይታወሳል።

አሰልጣኝ እያሱም ያለፉትን አስራ አንድ ሳምንት ጨዋታዎችን በጊዜያዊነት በመምራት ቡድኑን ከነበረበት የወራጅ ስጋት በማራቅ የተረጋጋ ውጤታማ ቡድን አድርገውት ቆይተዋል። ይህን የተረዱት የክለቡ አመራሮች አሰልጣኝ ኢያሱን ከጊዜያዊ አሰልጣኝነት ከፍ በማድረግ የቡድኑ ቋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸውን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ለሶከር ኢትዮጵያ ማምሻውን ያደረሱት መረጃ ያመላክታል።