በሊጉ ለመትረፍ ፍልሚያ ላይ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች አዲስ ሹመት ለማፅደቅ ከጫፍ ደርሰዋል።

ቀደም ብለው ከአሰልጣኝ ፀጋይ ኪዳነማርያም ጋር የተለያዩት መቐለ 70 እንደርታዎች በቀሪ የውድድር ዓመቱ ጨዋታዎች በሊጉ የሚያተርፋቸውን ውጤት ለማስመዝገብ አሰልጣኞችን በማነጋገር ላይ ከቆዩ በኋላ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በቴክኒካል እና የአካል ብቃት ጉዳዮች አማካሪነት ወደ አሰልጣኞች ቡድናቸውን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል።
ላለፉት ቀናት በሁለቱም ወገኖች በኩል የተደረገው ውይይት በስምምነት የተቋጨ ሲሆን አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በቀጣይ ቀናት ሥራቸውን እንደሚጀምሩም ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠናል። አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በሲዳማ ቡና በዋና እና በረዳት አሰልጣኝነት ጨምሮ በአዳማ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ በዋና አሰልጣኝነት መሥራታቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአሰልጣኝነት ፍቃድ ጋር በተያያዘ በቴክኒካል እና የአካል ብቃት ጉዳዮች አማካሪነት ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርተዋል።

