ከፈረሰኞቹ ጋር የነበራቸውን ውል ያጠናቀቁት
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ከስምምነት ደርሰዋል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሰልጠን የቆዩት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከፈረሰኞቹ ጋር ያላቸውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስማቸው ከሌሎች ክለቦች ጋር ሲያያዝ ከቆየ በኋላ ሀድያ ሆሳዕናን ለማሰልጠን ከስምምነት ደርሰዋል።
ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ብዙ ስኬቶችን ያገኘበትን ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨምሮ ባህር ዳር ከተማ ፣ አዳማ ከተማ እና መቻል ማሰልጠን የቻለው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የነብሮቹ አሰልጣኝ ለመሆን በቀጣይ ቀናት በይፋ ፌርማውን እንደሚያኖር ታውቋል።

